ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለሰባት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መውደቅ ምክንያት ሆኗል

ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለሰባት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መውደቅ ምክንያት ሆኗል

በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ከተማ አቅራቢያ ትናንት ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀን 8፡50 አካባቢ ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ  2 ሪጅን አስታወቀ።

በሪጅኑ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጎሳዬ ደምሴ እንዳስታወቁት ንፋሱ ከአዳማ 2 – አዋሽ ሰባት የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የሚሸከሙ ሰባት የብረት ምሰሶዎችን ጥሏል፡፡

አሁን ጉዳት በደረሰባቸው የብረት ምሰሶዎች አቅራቢያ ሁለት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በተፈጸመባቸው ስርቆት ከሳምንታት በፊት መውደቃቸውን አስታውሰዋል።

እንደ ሥራ አስኪጁ ገለጻ አሁን ላይ የወደቁት ሰባት ምሰሶዎች ቀደም ሲል  የተሰረቁትን ሁለት ምሰሶዎች ጠግኖ መስመሩን ኃይል ለመስጠት እየተሰራ ባለበት ወቅት መሆኑ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል።

የደረሰውን ችግር ስፋት ለመለየት እና የወደቁትን የብረት ምሰሶዎች ለመጠገን እንዲቻል የጥገና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልጸዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top