ለወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ ተቀያሪ ትራንስፎርመር እየተጓጓዘ ነው

ለወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ ተቀያሪ ትራንስፎርመር እየተጓጓዘ ነው

የቴክኒክ ችግር ለገጠመው የወልቂጤ ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ከአዲስ አበባ ተቀያሪ ትራንስፎርመር እየተጓጓዘ ነው።

230/66/33/15 የሆነው ትራንስፎርመር ዛሬ ማምሻውን ደቡብ ምዕራበ ሸዋ ዞን ወሊሶ ከተማ ደርሷል።

በማከፋፈያ ጣቢያው ትራንስፎርመሩን ለማስቀመጥ የሚያስችል የመሰረት ግንባታ፣ ከትራንስፎርመሩ ጋር የሚገናኙ ሽቦዎች ዝርጋታ እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

ትራንስፎርመሩ ችግር የገጠመውን ባለ 230/66/15 በመተካት ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች ኃይል በፍጥነት እንዲያገኙ  ያስችላል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስፎርመሩ ሲጓጓዝ መንገድ በማስከፈት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉት የፌደራል ፖሊስ፣ የሸገር ከተማ ፖሊስ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምስጋናውን ያቀርባል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top