የማከፋፈያ ጣቢያዎች ደህንነት – ለሕይወትና ለንብረት!

የማከፋፈያ ጣቢያዎች ደህንነት – ለሕይወትና ለንብረት!

የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለምን ልዩ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ?
የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ቮልቴጅ የሚያስተላልፉ መስመሮች ያሉበት አካባቢ በመሆኑ ጥንቃቄ የሚሹ ማዕከላት ናቸው። እነዚህ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ የቮልቴጅ መጠን ያለው ኃይልን ተቀብለው ለከተሞች፣ ለኢንዱስትሪዎች እና ለቤት ደንበኞች ደህንነቱ የተጠበቀ ዝቅተኛ ቮልቴጅ የሚያሰራጩ የኃይል ስርጭት ማዕከላት ናቸው። ጣቢያዎቹ ከኃይል ማመንጫዎች የሚመጣውን ከፍተኛ ቮልቴጅ በውስጣቸው ባሉ ትራንስፎርመሮችና ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት አስተካክሎ ለተጠቃሚው ማከፋፈል ያስችላል። ከፍተኛ ኃይልን ወደ ዝቅተኛ በመቀየር ለተጠቃሚው ለማሰራጨት የሚያግዙ ሲሆኑ በቂ ጥንቃቄ ካልተደረገ ግን ለሕይወት አደገኛ የኤሌክትሪክ ንዝረት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅራቢያ ምን ማድረግ አይኖርብንም?
📌 ያለፈቃድ ወደ ጣቢያው አንግባ።
አጥርን በመዝለል ወይም በመሹለክ ወደ ውስጥ መግባት ወይም የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን መንካት እጅግ አደገኛ ነው።

📌 በጣቢያዎች አቅራቢያ ሕንፃ አንገንባ።
የደህንነት ክልሎችን በመጠበቅ ለኃይል መሠረተ ልማቱም ሆነ ለሰዎች ደህንነት ተገቢውን ርቀት መጠበቅ ያስፈልጋል።

📌 እንጨት፣ የግንባታ ዕቃዎችን ወይም ተቀጣጣይ ነገሮችን አናከማች።
🔥 እነዚህ ነገሮች የእሳት አደጋን ሊያስከትሉ እና የጣቢያውን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ።

📌 በጣቢያው አቅራቢያ የሚኖር የእንቅስቃሴ ጨዋታን እንገድብ።
ልጆች ኳስ ሲጫወቱ መጫወቻዎችን ወደ ጣቢያው ሊወረውሩ ወይም አጥር ላይ በመውጣት አንዳንድ አደገኛ ተግባራትን ሊፈጽሙ ስለሚችሉ ወላጆችና አሳዳጊዎች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

📌 በአቅራቢያው ዛፎችን አንትከል።
🌳⚡️ የተክሎች እድገት ለኃይል መስመሮችና ለመሣሪያዎች አደጋ ሊፈጥር ስለሚችል ተገቢው ርቀት መጠበቅ ያስፈልጋል።

📌 የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን እንከተል።
⚠️🚫 “ከፍተኛ ቮልቴጅ”፣ “አደገኛ” እና ሌሎች የደህንነት ምልክቶች በቀላሉ የሚታዩ እና ያለምንም ምክንያት የማይታለፉ መልዕክቶች ናቸው።

⚠️ ከፍተኛ ቮልቴጅ ለምን የተለየ ጥንቃቄ ይፈልጋል?
⚡️ ከፍተኛ ቮልቴጅ ያለባቸው መሣሪያዎች ሳይነኩም አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
🚫 ስለዚህ “እነካዋለሁ ብቻ” ወይም “በአጥሩ አጠገብ ብቻ ነው የምቆመው” የሚል አመለካከት አደገኛ ነው።
🛡 ከፍተኛ ቮልቴጅ ካለበት ቦታ ርቀትን መጠበቅ ሕይወትን መጠበቅ ነው።

📢 ⚡️ የወደቀ የኃይል መስመር፣ ጉዳት የደረሰበት የኤሌክትሪክ ቁስ ከተመለከቱ፡
🚧 አይቅረቡ። 🚫
✋ አይንኩት።
📢ሌሎችንም እንዳይቀርቡ ያስጠነቅቁ።
📞ለሚመለከተው አካል በአስቸኳይ ያሳውቁ።

🇪🇹⚡️ የኃይል መሠረተ ልማት የጋራ ኃላፊነታችን ነው!
የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ሌሎች የኃይል መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ የኃይል አገልግሎቱ እንዲቀጥል ብቻ ሳይሆን የሰዎችን ሕይወት ❤️፣ ንብረት 🏠 እና ሀገራዊ ሀብት 🇪🇹 ለመጠበቅ ወሳኝ ነው።

🤝 የጋራ ንብረታችንን እንንከባከብ፤ ደህንነታችንንም እናስቀድም!

Scroll to Top