የማከፋፈያ ጣቢያው የፍተሻና የሙከራ ሥራ በስኬት ተጠናቋል

የማከፋፈያ ጣቢያው የፍተሻና የሙከራ ሥራ በስኬት ተጠናቋል

የደብረ ታቦር ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና የማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የፍተሻና የሙከራ ሥራ በስኬት መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ገለጹ።

ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ ከፈለኝ  እንደተናገሩት የማከፋፈያ ጣቢያው ለደብረ ታቦርና አካባቢው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ሰኔ 2015 ዓ.ም ነበር ግንባታው የተጀመረው።

የማከፋፈያ ጣቢያው የፍተሻና የሙከራ ሥራ ትናንት በስኬት መከናወኑን እና በዛሬው ዕለትም ትራንስፎርመሩን ሥራ የማስጀመር ሥራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

የማከፋፈያ ጣቢያው 100 ነጥብ 8  ሜጋ ዋት ኃይል የመሸከም አቅም ያላቸው ሁለት ባለ 63 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች እንዲሁም አስር ባለ 15 እና አስር ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች እንዳሉት አቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የግንባታ ሂደት የፀጥታ ስጋት እንዲሁም የዕቃ አቅርቦት ችግሮች አጋጥመውት የነበረ ቢሆንም ግንባታው በተያዘለት መርሀግብር መጠናቀቁ እንደ ታላቅ ስኬት እንደሚነሳ ተናግረዋል።

የደብረ ታቦር ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ መጀመር  ደብረ ታቦር ከተማ እና አካባቢው አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያነቃቃ አስረድተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top