የመቆጣጠሪያ ክፍሉ ዕድሳት እየተደረገለት ነው

የመቆጣጠሪያ ክፍሉ ዕድሳት እየተደረገለት ነው

በምሥራቅ 1 ሪጅን በመቶ ቀን ዕቅድ ከተያዙት ሥራዎች መካከል አንዱ የሆነው የድሬዳዋ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ የመቆጣጠሪያ ክፍል ዕድሳት እየተደረገለት መሆኑን የጣቢያው ኃላፊ ገለጹ።

ኃላፊው አቶ ሚካኤል አልዬ እንደገለጹት የመቆጣጠሪያ ክፍሉ ጣሪያ በዕድሜ ብዛት የተነሳ በመሠነጣጠቁ ፍሳሽ ወደ መቆጣጠሪያዎች በማስረግ ጉዳት እንዳያደርስ ዕድሳት እየተከናወነለት ነው።

ዕድሳቱ በዋናነት በመቆጣጠሪያ ክፍሉ ጣሪያ ላይ እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ይህም የዝናብ ውሃ በማስገባት መቆጣጠሪያዎቹን እንዳይጎዳ እና በጣቢያው የኦፕሬሽን ሥራ ላይ ጫና እንዳያሳድር ያደርጋል ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ  የመቆጣጠሪያ ክፍሉ የአርማታ ንጣፍ ሙሊት እና  የልሰና ሥራ ሲጠናቀቅ የውሃ መከላከያ ንጣፎችን ጨምሮ ሌሎች የማጠናቀቀያ ሥራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃሉ።

የድሬዳዋ ቁጥር 1 ማከፋፈያ ጣቢያ ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተደረገለት የማስፋፊያ እና የአቅም ማሳደግ ሥራ እስከ 56 ሜጋ ዋት ኃይል የመጫን አቅም አለው።

ጣቢያው በ15 ኪሎ ቮልት ባሉት ስድስት ወጪ መስመሮች ለድሬዳዋ ከተማ እና በዙሪያው ለሚገኙ ፋብሪካዎች እንዲሁም በ132 ኪሎ ቮልት ለናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ አስተማማኝ ኃይል እያቀረበ ይገኛል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top