በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ጉዳቶች ከኢኮኖሚ የዘለለ እንድምታ እንዳላቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ገለፁ፡፡
በተቋሙ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ስርቆቶችን በመከላከል ሂደት የተከናወኑ ሥራዎች ተገምግሟል።
በተቋሙ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደገለጹት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ጉዳቶች ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር ፓለቲካዊ አንድምታ ይኖራቸዋል፡፡
አንዳንድ ድርጊቶችም ያልተገባ ፓለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ታስቦ የሚከናወኑ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
ተቋሙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋት የሚያከናውነው ሥራ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚከናወን በመሆኑ በመሰረተ ልማቶቹ ላይ የሚፈፀመው ጉዳት እና የመልሶ ጥገና ሥራው ተቋሙን ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስወጣው አስረድተዋል፡፡
በተቋሙ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ድርጊቶችን በዘላቂነት ለመከላከል እንዲቻል በሪጅኖች የተሠማሩ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር አባላት የሚያከናውኗቸው ሥራዎች ተስፋ ሰጭ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በየአካባቢው ከሚገኙ የህብረተሰብ ተወካዮች እና የመስተዳደር አካላት ጋር የሚደረጉ የቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቋም ደህንነት መመሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው የተቋሙን መሠረተ ልማቶች ለመጠበቅ በመምሪያው ሥር የተዋቀሩ የመሠረተ ልማት ጥበቃ አባላት በተመደቡበትሪጅን ያለውን ሂደት የተመለከተ ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



