የመሠረተ ልማት ጥበቃ እና ስርቆትን መከላከል – የጋራ ኃላፊነት!

የመሠረተ ልማት ጥበቃ እና ስርቆትን መከላከል – የጋራ ኃላፊነት!

የኃይል መሠረተ ልማቶች የጋራ ንብረታችን ናቸው!
የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች በሕዝብ ሀብት የተገነቡ እና ከፍተኛ ሀብት የፈሰሰባቸው የሀገር ንብረቶች ናቸው። የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ የማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ የማስተላለፊያ መስመሮችና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ኃይል ለቤተሰቦች፣ ለኢንዱስትሪዎች፣ ለንግድና ለሌሎች ተጠቃሚዎች እንዲደርስ የሚያስችሉ ናቸው።

🚨 የኃይል መሠረተ ልማት ስርቆት ምን ጉዳት ያስከትላል?
🔌 የኃይል አቅርቦትን ሊያስተጓጉልና አገልግሎት እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል።⏱️
💰 የተሰቀውን ለመጠገንና መልሶ ለመተካት ከፍተኛ ወጪ ያስከትላል።
🏭 የንግድና የኢንዱስትሪ ሥራዎችን ያስተጓጉላል።
🇪🇹 የሀገር ሀብትን ለብክነት ያጋልጣል።

👥 ሕብረተሰቡ ምን ማድረግ ይችላል?
👀 በኃይል መሠረተ ልማቶች አካባቢ አጠራጣሪ እንቅስቃሴን መከታተል፤
📢 የተበላሸ መስመር፣ ምሰሶ ወይም መሣሪያ ሲያይ ለሚመለከተው አካል በፍጥነት ማሳወቅ፤
🚫 ስርቆትን አለመደገፍ፤ የተሰረቀ የኃይል መሰረተ ልማትን አለመግዛት፤
🤝 ከሚመለከታቸው ተቋማትና ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር መተባበር።

🛡 የተገነባውን መጠበቅ የልማቱ አካል መሆን ነው!
እንደ ሀገር የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን መገንባት ያስፈልጋል። እነዚህን የጋራ ንብረቶች ከጉዳትና ከስርቆት መጠበቅም እንዲሁ የሁላችንም ድርሻ ነው።
⚡️ እንገንባ።
🛡 እንጠብቅ።
🤝 እንተባበር።
📢 አደጋንና ስርቆትን እናሳውቅ።
🇪🇹 የጋራ ንብረታችንን እንንከባከብ፤ የኃይል አገልግሎታችንን እናስቀጥል!

Scroll to Top