ሠራተኛው የሥነ ምግባር መርሆዎችን በማክበር ሥራውን ማከናወን አለበት

ሠራተኛው የሥነ ምግባር መርሆዎችን በማክበር ሥራውን ማከናወን አለበት



ሠራተኞች ከሥራ ሥነ- ምግባር አጣብቂኞች ነፃ በመሆን እና የሥነ ምግባር መርሆዎችን በማክበር ሥራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥነ- ምግባርና የፀረ- ሙስና መምሪያ ዳይሬክተር ተናገሩ።

ዳይሬክተሩ አቶ ደረጀ አጥናፌ ለተቋሙ የሦስተኛ ዙር ሠልጣኞች “በሥራ ቦታ ሥነ-ምግባር ” ዙሪያ ስልጠና በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት አንድ ተቋም በማህበረሰቡና በደንበኞች ዘንድ አመኔታና መልካም ስም እንዲኖረው ለማድረግ ጠንካራ የሥራ ሥነ- ምግባር ባህል መገንባት ያስፈልጋል።

ለዚህም ማንኛውም የተቋም ሥራዎች የሥራ ቦታ ሥነ- ምግባር መርሆዎችንና ሌሎች ሕግጋትን ባከበረ አግባብ መከናወን እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በተቋም የሥራ ሥነ- ምግባር ሲከበር ምቹ የሥራ ከባቢ እንዲፈጠር በማድረግ ሠራተኞች ክብር፣ ደህንነትና ተነሳሽነት እንዲሰማቸው ከማድረግ ባለፈ ብቃት ያላቸው አዳዲስ ባለሙያዎች ወደ ተቋሙ እንዲሳቡ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የተቋሙ መልካም ስም እንዳይጠፋ ሠራተኞች የሥራ ሥነ- ምግባር አጣብቂኞችን በመለየት ሕግን አክብሮ መስራት እንደሚገባቸው ነው የጠቀሱት።

የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ገፅታውን ለመገንባትና በሠራተኛው መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የሠራተኞች የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀም የተቋሙን እሴቶች፣ የአሰራር መመሪያዎች እና የሥነ ምግባር መርሆዎችን በተላበሰና በጠበቀ መልኩ መሆን እንደሚገባውም አሳስበዋል።

Scroll to Top