አንድ የማስተላለፊያ መስመር ወይም ምሰሶ ስርቆት ምን ሊያስከትል ይችላል?

አንድ የማስተላለፊያ መስመር ወይም ምሰሶ ስርቆት ምን ሊያስከትል ይችላል?

ስርቆት የሚፈፀምበት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግብዓት በመጠኑ አነስተኛ ኪሳራ ብቻ የሚያስከትል ቢመስልም ተፅዕኖው ግን ከተሰረቀው ዕቃ ዋጋ እጅግ የሚያልፍ ማኅበረሰባዊ ችግር ሊሆን ይችላል። የተሰረቀ የኃይል መሠረተ ልማት የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ሊያስተጓጉል፣ ቤተሰቦችንና ንግዶችን ሊጎዳ፣ የትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን ሥራ ሊያስተጓጉል እና እርሱን ለመጠገንና ለመተካት ተጨማሪ ወጪ ሊያስከትል ይችላል። የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋትና አዳዲስ የኃይል መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ስንሠራ ቀድሞ የተገነባውን መጠበቅም እኩል አስፈላጊ ነው።

🌍 የተገነባውን መሠረተ ልማት መጠበቅ የልማቱ አካል መሆን ነው!
አዳዲስ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ሌሎች የኃይል መሠረተ ልማቶችን መገንባት ከፍተኛ ኢንቨስትመንትና ቀጣይነት ያለው ጥረት ይጠይቃል። ይሁን እንጂ ልማት መሠረተ ልማት በመገነረባት ብቻ አያበቃም። እነዚህ ንብረቶች ሲሰረቁ የሚደርሰው ጉዳት ከእቃው የገበያ ዋጋ እጅግ የሚያልፍ ነው። የአንድ ኬብል ወይም የአንድ መሣሪያ ስርቆት ከአገልግሎት መቋረጥ እስከ ተጨማሪ የጥገናና የመተካት ወጪ ድረስ ተከታታይ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

👥 ሕብረተሰቡ ምን ማድረግ ይችላል?
በኃይል መሠረተ ልማት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ከእነዚህ አገልግሎቶች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። ስለዚህ የጋራ ንብረቶቻችንን መጠበቅ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ይፈልጋል።

👀 ንቁ እንሁን!
በማስተላለፊያ መስመሮች፣ በማከፋፈያ ጣቢያዎች ወይም በሌሎች የኃይል ተቋማት አካባቢ የሚታዩ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ችላ አንበል።

📢 አጠራጣሪ ሁኔታዎች ስንመለከት እናሳውቅ!
የተበላሸ ወይም የተነካካ የኃይል መስመር፣ ምሰሶ፣ ኬብል ወይም ሌላ መሣሪያ ካየን፣ በፍጥነት ለሚመለከተው አካል እናሳውቅ።

🚫 ስርቆትን አንደግፍ!
የተሰረቀ የኤሌክትሪክ ግብዓት አንግዛ። የተሰረቁ የመሠረተ ልማት እቃዎችን እንደ መደበኛ ዕቃ መግዛት ተጨማሪ ስርቆትን ሊያበረታታ ይችላል።

🤝 እንተባበር!
የኃይል መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ ከሚመለከታቸው ተቋማትና ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር እንተባበር።

🛡 ይህን መሠረተ ልማት እንደ የጋራ ንብረታችን እንጠብቅ!
አንድ ሰው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶን ወይም የማስተላለፊያ መስመርን ሲጎዳ ወይም ሲሰርቅ ተፅዕኖው በአንድ ተቋም ንብረት ላይ ብቻ ተገድቦ የሚቀር አይደለም።
🏠 ቤተሰቦች ይጎዳሉ።
🏫 ትምህርት ቤቶች ይጎዳሉ።
🏥 የጤና ተቋማት ይጎዳሉ።
🏭 ኢንዱስትሪዎች ይጎዳሉ።
💼 የንግድ ተቋማት ይጎዳሉ።
የሀገር ሀብትም ይጎዳል።
ስለዚህ ይህን አመለካከት እንገንባ “ይህ የሌላ ሰው ንብረት አይደለም፤ የጋራ ንብረታችን ነው።” የሚል፡፡

Scroll to Top