የህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም

የህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አይደለም

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የገነባችው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በውሃ ሀብታችን የመጠቀም ጅማሮ መሆኑንና ገና በርካታ ሥራዎች ሊከናወኑ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምሕንድስና መምህሩ ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ይልማ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ ገና መጠቀም ጀመረች እንጂ የማንንም ጥቅም የነካች ባለመሆኑ የህዳሴ ግድብን መገንባቷ ምንም ዓይነት ቅሬታ የሚያስነሳባት ጉዳይ አይደለም።

የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ተራራማ ሥፍራዎች የሚነሳ የተፈጥሮ ሀብቷ ቢሆንም የታችኛውም ሆነ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በሚጠቅምና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ያስቀመጠችው እውነታ እንደሆነም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የውሃ አጠቃቀም ሕግ የተላለፈችበት ጊዜ እንደሌለ የገለጹት ፕሮፌሰር ይልማ አሁንም ቢሆን ፍትሐዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ወንዙን ለሌሎች አገልግሎቶች የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት አስረድተዋል።

የግብፅ ጩኸት የውሃ መጠን ቀንሶባት ሳይሆን ቀደም ሲል በበላይነት የመጠቀም አሠራሯ እንዳያበቃ ከመስጋት የመነጨ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አክለው ገልጸዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

Scroll to Top