የህብረተሰቡን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ የጋራ አሰራር መዘርጋት ይገባል

የህብረተሰቡን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ የጋራ አሰራር መዘርጋት ይገባል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ የሚተገብሯቸው አሰራሮች የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ጥያቄ የሚመልሱ እንዲሆን የማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽን ዘርፍ አሳሰበ፡፡

በዘርፉ የማዕከላዊ 3 ሪጅን እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አባባና የሸገር ከተማ የዲስትሪዩቢሽን ኃላፊዎች የ100 ቀናት ዕቅዶቻቸዉ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የሪጅኑ የጥገና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ  ታደሰ  ገብሬ  እንደገለፁት የውይይቱ ዓላማ በኦፕሬሽን እና ጥገና ሥራዎች የአፈፃፀም መሥፈርት /SOP/ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ፣ ደንበኞችን ማዕከል ያደረገ የተቀላጠፈ ሥራ ለመስራት እና የኃይል  ጭነትን ለማሻሻል ነው፡፡

በውይይቱ ላይ በሪጅኑ ውስጥ በሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በ15 እና በ33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች በአዲስ አባባና በሸገር ከተማ ላይ የሚታዩ የኃይል መቆራረጥ ችግሮችን በጋራ መፍታት እና የጋራ አሰራሮችን ማበልፀግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡

በ100 ቀናት ዕቅዱ ላይ የተካተቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ መግባባት ፈጥሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቶ ታደሰ አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን የፕላኒንግ ኃላፊ የሆኑት አቶ አለነ ወልዴ በበኩላቸው የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረትና ከአቅም በላይ ጭነት ያለባቸው መስመሮች መኖራቸውን ለሥራቸው እክል እንደሆነ ተናግረዋል።

የውይይት መድረከ  ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡     

እንደ አቶ አለነ ገለፃ ተቋማቱ በጋራ የሚሰሯቸዉን ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጉ ይገባል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top