የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን የእርስ በእርስ ትውውቅ የትውውቅ መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
በተቋማቱ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የተመደቡ የሥራ ኃላፊዎችን እርስ በእርስ ለማስተዋወቅ ትናንት ምሽት በተዘጋጀ መርሃግብር ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት በመተጋገዝና ተቀራርቦ በመሥራት በዘርፉ የሚነሳውን ችግር በጋራ መፍታት ይቻላል፡፡
ግንኙነቱ የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን እርካታ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ጌዜ ሳይጠብቁ ለመነጋገር ዕድል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው የሁለቱ ተቋማት ግንኙነት ኃይል ከመሸጥና ከመግዛት ያለፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እንደዚህ ዓይነት የግንኙነት መድረኮች የበለጠ የሚያቀራርቡ እና ፈጣን መፍትሔ ለመስጠት የሚያግዙ በመሆናቸው በመደበኛ አሰራሮች ታግዘው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
