የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ

የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች የደዴሳ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያን ዛሬ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የፌዴራል  ፖሊስ የምዕራብ ኦሮሚያ አዛዥ ኮማንደር ማሙዬ አባተ እንዳሉት የተቋሙ አመራሮች በግዳጅ ላይ ያሉትን የሠራዊት አባላት መጎብኘታቸው ለሠራዊቱ አባላት የሞራል ጥንካሬ ይሰጣል።

ማከፋፈያ ጣቢያው በረሃማ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የውሃ አቅርቦት እንዲስተካከል እና የወባ መከላከያ አጎበር እንዲሰጣቸው እንዲሁም የጥበቃ ማማ እንዲገነባላቸው ጠይቀዋል።

በተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ደህንነትና ቁጥጥር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደተናገሩት ተቋሙ ከፌደራል ፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የመሠረተ ልማት ስርቆትን ለመከላከል በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

በሠራዊቱ አመራሮች ለቀረቡት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር እንደሚነጋገሩም ገልፀዋል።

በተቋሙ የንብረት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው  ለጥበቃ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የንብረት ማስቀመጫ መጋዘን ለመገንባት መታቀዱንና ያልተሟሉ ፋሲሊቲዎችን ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመነጋገር ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top