ዘርፉ የግማሽ ዓመቱን አፈፃፀም ገመገመ

ዘርፉ የግማሽ ዓመቱን አፈፃፀም ገመገመ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ የተሽከርካሪ ስምሪትና አስተዳደርን የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በመገምገም ከአሽከርካሪዎች ጋር ተወያየ።

ውይይቱን የመሩት የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው እንደገለጹት  መድረኩ የተቋሙን ስትራቴጂክ ግቦች መሰረት የተዘጋጀው በሥራ ክፍሉ የተከናወኑ ተግባራትን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን እንዲሁም የሥራ ላይ ምክክር ለማድረግ ታስቦ ነው፡፡ 

ሥራ አስፈፃሚዋ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት የሥራ ክፍሉ በግማሽ ዓመቱ 396 የተሸከርካሪ አገልግሎት ጥያቄ ቀርቦለት ለ241 ጥያቄዎች ምላሽ መስጠቱን እና ለ104 ተሸከርካሪዎች የቴክኒክ ምርመራ ለማድረግ አቅዶ ለ108 ተሽከርካሪዎች ምርመራ ማድረጉን ገልፀዋል።

ወጪን ከመቀነስ አኳያ በሥራ ክፍሉ በሚገኙ የፑል ተሸከርካሪዎች ላይ በተደረገው የነዳጅ ቁጥጥር 1274 ሊትር ነዳጅ በመቀነስ ከ109,974 ብር በላይ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በግምገማው ላይ ከጂ.ፒ.ኤስ. አጠቃቀም፣ ከተሽከርካሪ ጥገና፣  ከጋራዥ አገልግሎት አሰጣጥ እና ከሥራ ክፍሉ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ጥያቄዎች ከሠራተኞች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ከጂ.ፒ.ኤስ. አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሥራ አስፈፃሚዋ ጂ.ፒ.ኤስ. በተሸከርካሪዎች ላይ መገጠሙ የተሽከርካሪ አስተዳደር አሰራር ን ማዘመኑን ገልፀዋል።

ቴክኖሎጂው ተሽከርካሪዎች የት እንዳሉ ለማወቅ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ አዘዋውሮ ለማሰራት፣ የነዳጅና ጎማ አጠቃቀምን ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር እንዳስቻለ አስረድተዋል።

እንደ ወ/ሮ ስመኝ ገለፃ የቴክኖሎጂው መተግበር የተቋሙ ተሽከርካሪዎችን የፍጥነት ገደብን በመወሰን አደጋን ለመቀነስ፣ ተሸከርካሪዎች የሄዱበትን አቅጣጫና ምን ያህል ኪሎ ሜትር እንደተጓዙ በማሳየት የተቋሙን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል አስችሏል።

የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች ከሠራተኞች ለተነሱት ጥያቄዎቹ ተጨማሪ ማብራሪያና አስተያየት ሰጥተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top