ተቋማቱ የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል በጋራ ተስማሙ

ተቋማቱ የኃይል አቅርቦትን ለማሻሻል በጋራ ተስማሙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለህብረተሰቡ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ በሚያስችሉ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

የሁለቱን ተቋማት የጋራ ውይይት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ መርተውታል።

በሁለቱ ተቋማት የተለዩና መፍትሄ የተበጀላቸው ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በአዲስ አበባና በሌሎችም ከተሞች የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ በተሰሩና መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ቀርቧል።

ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለቅድመ መከላከል ጥገናም ሆነ ለማሻሻያና መልሶ ግንባታ ሥራ የሚቋረጥ ኃይል ላይ ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ተቋማቱ የሚሰጡት አገልግሎት ለሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ በሠራተኞች ዘንድ ተመሳሳይ ግንዛቤ መያዝ እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top