በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ገቨርናንሰ እና ኮምፕሊያንስ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን መገምገም ጀምሯል።
የዘርፉ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ድጉማ ነዳ እንደገለጹት ግምገማው በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ያልተከናወኑ ሥራዎቸ ደግሞ በቀሪዎቹ ሦስት ወራት በማጠናቀቅ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ያለመ ነው።
ግምገማው በዋነኛነት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተቋሙን ጥቅምን ለማስጠበቅ፣ የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት እና በተቋሙ ውስጥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ የተከናወኑ ሥራዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
ግምገማው የዘርፉን የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


