ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተቋም ደረጃ እየተከበረ ነው

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በተቋም ደረጃ እየተከበረ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በተገኙበት ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን በዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ እያከበረ ይገኛል።

መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለፁት ሁሉም የሥራ መሪና ሠራተኞች የዕለት ከዕለት ስራዎችን ሲያከናውኑ ሥነ ምግባርን በመላበስ እና ህጋዊ የአሰራር ሥርዓት በተከተለ መንገድ መሆን ይኖርበታል።

ኢንጅነር አሸብር ባልቻ
ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ

የዘንድሮው የፀረ- ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑንም ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው የገለፁት።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top