ከጥልቁ ምድር የሚገኝ የማይነጥፍ የኃይል በረከት – የከርሰ ምድር እንፋሎት (Geothermal)! 🇪🇹⚡️

ከጥልቁ ምድር የሚገኝ የማይነጥፍ የኃይል በረከት – የከርሰ ምድር እንፋሎት (Geothermal)! 🇪🇹⚡️

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በመገኘቷ ከፍተኛ የከርሰ ምድር እንፋሎት ወይም የጂኦተርማል ኃይል እምቅ አቅም ካላቸው ጥቂት ሀገራት አንዷ ናት። ይህንን በመጠቀም ረገድ እንደ ሀገር የአሉቶ ላንጋኖ የጂኦተርማል ፕሮጀክት እንደ ዓይን ከፋች ፕሮጀክት ተደርጎ የሚወሰድ ቢሆንም በዘርፉ ብዙ መስራት እንዳለብን የሚያሳይ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ በአሉቶ እስከ 70 ሜጋ ዋት ለማመንጨት የማስፋፊያ ፕሮጀክት እየተከናወነ ሲሆን እንደ ቱሉ ሞዬ እና ኮርቤቲ ባለ ሳይቶች የግል አልሚዎች በዘርፉ ለመሰማራት የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

⚙️ የኃይል አመራረት ሂደቱ እንዴት ነው?

የጂኦተርማል ኃይል አመራረት ሂደት ተፈጥሮንና ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ የሚሠራ አስደናቂ ሂደት ነው፡፡ ዋና ዋና ሂደቶቹም፡-

  1. ቁፋሮ፦
  2. በመጀመሪያ ጥልቅ የሆኑ ጉድጓዶች (Wells) እስከ ሦስት ሺህ ሜትር ድረስ ወደ መሬት ውስጥ ይቆፈራሉ።
  3. የእንፋሎት መውጣት፦
  4. ከመሬት በታች ያለው ከፍተኛ ሙቀት በውስጥ ያለውን ውሃ ወደ ትኩስ እንፋሎት ይቀይረዋል። ይህ ከፍተኛ ግፊት ያለው እንፋሎት በትቦዎች አማካይነት ወደ ላይ ይወጣል።
  5. ተርባይን ማሽከርከር፦
  6. ወደ ላይ የወጣው እንፋሎት ግዙፍ ተርባይኖችን በከፍተኛ ፍጥነት ያሽከረክራል።
  7. ኤሌክትሪክ ማመንጨት፦
  8. ተርባይኑ ሲሽከረከር ከጄነሬተር ጋር በመገናኘት ሜካኒካዊ ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ይቀይራል።
  9. መልሶ መጠቀም፦
  10. ጥቅም ላይ የዋለው እንፋሎት ተመልሶ ወደ ውኃነት እንዲቀየር ተደርጎ ወደ መሬት ውስጥ ተመልሶ በመርፌ (Injection) መልክ ይገባል፤ ይህም ሂደቱ ተደጋጋሚና ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል።

🌟 የጂኦተርማል ኃይል ዋና ዋና ጥቅሞች፦

🌋   ከአየር ንብረት ጋር አለመለዋወጡና አስተማማኝነቱ (Reliability)፦

  • እንደ ውኃ ግድቦች በዝናብ እጥረት፣ ወይም እንደ ፀሐይና ነፋስ በአየር ሁኔታ አይቀያየርም። በቀን 24 ሰዓት፣ በዓመት 365 ቀናት ያለ ማቋረጥ ኃይል ይሰጣል።

🌋   ታዳሽና ንጹሕ ኃይል መሆኑ፦

  • ምንም ዓይነት ተረፈ ምርት ወይም በካይ ጋዝ ስለማያመነጭ ለአካባቢ ጥበቃና ለ”አረንጓዴ ኢኮኖሚ” ግንባታ ተመራጭ ነው።

🌋   ዘላቂና የማይነጥፍ የኃይል ምንጭ መሆኑ፦

  • የከርሰ ምድር እንፋሎት ሁልጊዜም ያለ በመሆኑ ለዘመናት አገልግሎት የሚሰጥ ዘላቂ የኃይል ምንጭ ነው።

🌋   አነስተኛ ቦታ የሚፈልግ መሆኑ፦

  • ከውኃ ግድቦች ወይም ከሶላር ፓርኮች አንጻር ሲታይ በጣም አነስተኛ በሆነ የቆዳ ስፋት ላይ ሰፊ ኃይል ማመንጨት ይቻላል።

ሀገራችን በአሉቶ ላንጋኖ፣ በቱሉ ሞዬ እና በኮርቤቲ አካባቢዎች የጀመረቻቸው የጂኦተርማል ፍለጋና የማልማት ፕሮጀክቶች እውን ሲሆኑ የኃይል አቅርቦታችንን ይበልጥ አስተማማኝ እንደሚያደርጉት ይታመናል።

የኢትዮጵያ ብርሃን ከምድር ጥልቀት እስከ ሰማይ ከፍታ ይበራል!

Scroll to Top