የታንዛኒያ ኤሌክትሪክ አቅራቢ ድርጅት የእቅድ፣ ምርምር እና ኢንቨስትመንት ምክትል ዳይሬክተር ሚስስ ሬንታ ሲ ንድጌ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት እና ሌሎች የሥራ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡
ዳይሬክተሯ በጎብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ካምፓኒያቸው በኃይል አቅርቦት እና ተያያዥ ጉዳዮች ከተቋሙ ጋር በመስራቱ ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ወደ ተቋሙ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጡት ምክትል ዳይሬክተሯ የተቋሙ ሠራተኞች ልጆቻውን በመከባከብ በሥራ ቦታ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት ማቆያ እና የሰራተኞች ክሊኒክ መዘጋጀቱ የሚበረታታ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
የሁለቱ ተቋማት የኃይል ሽያጭ ስምምነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚለወጥ እምነታቸውን ገልፀዋል።
ተቋሙ በኃይል ልማቱ ዘርፍ ያለውን የካበተ ልምድና አቅም ለካምፓኒያቸው ባለሙያዎች በማጋራት የተቋማቱን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ያላቸውን እምነት ሚስስ ሬንታ ገልጸዋል ፡፡
ምክትል ዳይሬክተሯ በጉብኝታቸው የተቋሙን የህጻናት ማቆያ፣ የሠራተኞች ክሊኒክ፣ በግንባታ ላይ ያለውን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ፕሮጀክት እና የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ተመልክተዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”



