በተቋሙ የኤሌክትሪክ ተሸርካሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው

በተቋሙ የኤሌክትሪክ ተሸርካሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የገዛቸውን የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ አውቶቡሶች ወደ ሥራ ለማሰገባት የሚያስችል ስልጠና እየሰጠ መሆኑን በተቋሙ የትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር መምሪያ አሰታወቀ፡፡

የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ኃይላይ ተስፋይ እንደገለፁት ተቋሙ ለሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዘጠኝ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ገዝቷል፡፡

እነዚህን ተሸከርካሪዎች ወደ ሥራ ለማስገባት 35 ለሚሆኑ ሾፌሮች፣ መካኒኮችና ኤሌክትሪሽያኖች ለሦስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ በመጡ አሰልጣኞች መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ሥልጠናው ባለሙያዎቹ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ለማድረግ፣ ለመጠገንና ለማሽከርከር የሚስችላቸውን ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አቶ ኃይላይ ተናግረዋል፡፡

ከስልጠናው ቀጥሎ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ተሸከርካሪዎቹን ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ገልፀዋል፡፡

ሁለት የተሸከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች በዋና መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገንብተው ዝግጁ መሆናቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን መጠቀም መቻሉ ከተለያዩ ወጭዎች እንደሚያድነውም አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ለመግዛት ስምምነት ካደረገባቸው 12 ተሸከርካሪዎች መካከል አራት ከፍተኛና አምስት መካከለኛ አውቶብሶችን በቅርቡ በጊቢው ውስጥ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተካሄደ የርክክብ ፐሮግራም መረከቡ ይታወሳል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top