ከተቋሙ ዕሴቶች ጋር የተስማማ የስራ ዘዬ መከተል ይገባል ተባለ

ከተቋሙ ዕሴቶች ጋር የተስማማ የስራ ዘዬ መከተል ይገባል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ራሳቸውንና ተቋሙን ስኬታማ ለማድረግ  ከተቋም ዕሴቶች ጋር የተስማማ የስራ ዘዬ እንዲከተሉ የተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ቢሮ አሳሰበ።

ቢሮው ለተቋሙ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር የምክር ቤት አባላት በተቋም እና ሠራተኛ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ስልጠና በአዳማ ከተማ ሲሰጥ ሥራ አስኪያጁ አቶ አንዷለም ኪዳኔ እንደተናገሩት የአገልጋይነት ስሜት የተላበሰ የስራ ባህል በመፍጠር የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ ማሳካት ይገባል።

በየትኛውም የሥራ መስክ ስኬታማ ለመሆን የሙያ ክህሎትን እና ዕውቀትን ማበልፀግ፣ ፕሮፌሽናል አስተሳሰብ መገንባት እና የሥራ ፍቅርን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

ለደመወዝ እና ኃላፊ ለመሆን ሳይሆን ለተቋሙ ሁለንተናዊ ዕድገት እና ለህሊና መስራት እንደሚገባም ነው አቶ አንዷለም ያነሱት።

የተቋሙ የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ሊቀመንበር አቶ መኮንን ክፍሌ በበኩላቸው የምክር ቤቱ አባላት የሠራተኛውን ጥቅም ከማስጠበቅ ባሻገር ዘመኑን የዋጀ ዕውቀት፣ ክህሎትና አስተሳሰብ በማዳበር ለኃይል ልማት ዘርፉ እመርታ ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስኬታማ የቡድን ሥራ እውን ለማድረግም በዕውቀት የሚመራ ምክንያታዊ አሰራር  ማጎልበት እና መልካም የእርስ በእርስ ግንኙነት መፍጠር እንደሚገባ በስልጠናው ወቅት ተገልጿል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top