ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ለኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል

ከባድ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ ለኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ኦዳ በተባለ አካባቢ ከትናንት በስቲያ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ስድስት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች በመጣሉ ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የደቡብ 1 ሪጅን አስታወቀ።

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ንጉሴ እንዳስታወቁት ጉዳቱ የደረሰው ከመልካ ዋከና – ራይቱ – ጎዴ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ነው።

መስመሩ ለጎዴ እና ቀብሪደሃር ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኃይል የሚሰጥ ሲሆን ከእነዚህ ጣቢያዎች ኃይል የሚያገኙ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ኃይል መቋረጡን ገልፀዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ የወደቁ ታወሮችን መልሶ ለመጠገን የሪጅኑ የጥገና ሠራተኞች በስፍራው የደረሱ ሲሆን ሥራውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቀ ከዋና መስሪያ ቤት ተጨማሪ የጥገና ባለሙያዎች ወደ ሥፍራው መንቀሳቀሳቸውን ተናግረዋል።

ስለሆነም የወደቁት ታወሮችን በጊዜያዊነት በመጠገን ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መልሰው ኃይል እስከሚያገኙ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top