ላለፉት 18 ቀናት በሁመራ እና አካባቢው ተቋርጦ የቆየውን ኃይል መልሶ የማገናኘት ሥራ መጠናቀቁን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ውበት አቤ እንዳስታወቁት በአካባቢው ኃይል ተቋርጦ የቆየው ከሽሬ- ሁመራ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ተሸካሚ የብረት ምሰሶ በመውደቁ ነው።
ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ኃይል የተቋረጠባቸው ሁመራ ከተማን ጨምሮ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ አዲረመጥ፣ ሶረቃ፣ ማይካድራ፣ አብደራፊ፣ አብርሃጅራ፣ አዲጎሹ እና አደባይ የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አግኝተዋል።
ህብረተሰቡ የደረሰው ጉዳት እስኪጠገን ድረስ በትዕግስት በመቆየቱ እና በጥገና ሥራው ላይ ድጋፍ በማድረጉ አቶ ውበት አመስግነዋል።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”