አዲስ የተቋቋመው የተቋሙ ክበብ የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነቱን ተረከበ

አዲስ የተቋቋመው የተቋሙ ክበብ የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነቱን ተረከበ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሠራተኞች ክበብ አዲስ የመተዳደሪያ ደንብ ፀድቆ ወደ ተግባር መገባቱን የተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አስታወቁ።

ኃላፊው አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደተናገሩት እንደ አዲስ የተቋቋመው የሥራ አመራር ቦርድ ለሠራተኛው በቂ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል አሰራር መዘርጋት ይጠበቅበታል፡፡

ቦርዱ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት የሠራተኛውን ፍላጎት ለማርካት በርትቶ እንዲሠራ የተቋሙ ማኔጅመንት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ ሙላት አረጋግጠዋል፡፡

የተቋሙ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር አቶ መኮንን ክፍሌ በበኩላቸው ሠራተኛው ከሚያነሳቸው ቅሬታዎች አንዱ የካፍቴሪያ አገልግሎት መሆኑን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት አዲስ አደረጃጀት መዋቀሩን አስታውቀዋል።

የተቋሙ የሰው ኃይል ስራ አስፈፃሚ አቶ አታላይ አበበ እንደተናገሩት ኃላፊነቱ በዋናነት የተሰጠው ለመሰረታዊ የሠራተኛ ማህበሩ ቢሆንም የክበብ አገልግሎቱ እንዲጠናከር ተቋሙ ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ሠራተኛውን ማርካት፣የአሠራር ግልፀኝነት ማስፈንና ተራማጅ አሠራሮችን መተግበር ከቦርዱ እንደሚጠበቅ ያነሱት ደግሞ በዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮች እና ዶክመንቴሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ ናቸው፡፡

አዲስ የተሰየሙት የክበቡ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሌንሴ ኤድኤ በበኩላቸው አባላቱ የተጣለባቸው ኃላፊነት ከባድ መሆኑን ተረድተው በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የክበቡ ሥራ አመራር ቦርድ ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን የቦርድ ሰብሳቢዋ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ ሌንሴ ኤደኤ የክበቡን የመተዳደሪያ ደንብ ከተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ እጅ ተረክበዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top