እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት በርካታ ሥራዎች መሥራት ይገባል

እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት በርካታ ሥራዎች መሥራት ይገባል

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ እየመጣ ያለውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በርካታ ሥራዎች እየሰራ ይገኛል፡፡

በዓመት በአማካይ በ6 በመቶ እያደገ የሚሄደውን የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ የኢንዱስትሪ ደንበኞችን ፍላጐት ለማሟላት የኃይል አቅርቦቱ አሁን ካለበት 3 ሺህ 271 ጊጋ ዋት ሰዓት ወደ 5 ሺህ 205 ጊጋ ዋት ሰዓት ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡

በተመሳሳይ በየዓመቱ በአማካይ በ20 በመቶ እንደሚያድግ የተተነበየውን የመካከለኛና ዝቅተኛ ኢንዱስትሪዎች የኃይል አጠቃቀም አሁን ካለበት 739 ጊጋ ዋት ሰዓት ወደ 3 ሺህ 285 ጊጋ ዋት ሰዓት ማድረስ ይገባል፡፡

ከዚህ ባልተናነሰ በአገልግሎቱ ዘርፉ ውስጥ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና አስተማማኝነት ችግሮችን በማስወገድ፣ የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽና ቆይታና በማስተካከል የደንበኞችን እርካታ ማሻሻል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

እንደ ሀገር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ ኦፕሬሽንና ጥገና ወጪን ታሳበ ያደረገ ታሪፍ ቢተገበር አገልግሎቱን ለማሻሻልና ተደራሽነቱን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ይታመናል፡፡

Scroll to Top