በቀጣይ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ያለው የታሪፍ ምጣኔ እንቅፋት እንዳይሆን ስጋት ፈጥሯል

በቀጣይ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ያለው የታሪፍ ምጣኔ እንቅፋት እንዳይሆን ስጋት ፈጥሯል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በነደፈው የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለመገንባት ዕቅድ ይዟል፡፡

ከዕቅዶች መካከል አስራ ስድስቱ ፕሮጀክቶች የተቋሙን አሰራር ከማዘመን እና ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም ታስቦ የተቀረፁ ፕሮጀክቶች ሲሆን ፕሮጀክቶቹን ለማስፈፀም እስከ ዘጠና ስድስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል፡፡

በተቋሙ የሚተገበሩ ሰላሳ ሶስት የሚደርሱ የማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ደግሞ የሚያስፈልጋቸው የካፒታል መጠን 767 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡

በስትራቴጂክ ዕቅድ ዘመኑ በግል ባለሀብቱ ሊገነቡ በዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል ከአምስት የፀሀይ ፕሮጀክቶች 775 ሜጋ ዋት፤ እንዲሁም ከስድስት የንፋስ ፕሮጀክቶች 825 ሜጋ ዋት ለማመንጨት ታቅዷል፡፡

በግል ባለሀብቱ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች የሚያስፈልገው የካፒታል መጠንም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል::

እነዚህ ሁሉ እንዳሉ ሆነው አሁን ያለው በሀገሪቱ በሥራ ላይ ያለው የታሪፍ ምጣኔ አነስተኛ መሆንና የኦፕሬሽንና የጥገና ወጪን ለመሸፈን አለማሰቻሉ በትግበራው ላይ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ የግል አልሚውን ለመሳብ አስቸጋሪ እንዳይሆን ስጋት ፈጥሯል፡፡

Scroll to Top