ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን statistica የተሰኘ ድረ ገፅ ገልጿል፡፡

ድረ ገፁ ባሰፈረው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ አንጎላና ሊቢያ ለግለሰብ ተጠቃሚዎች በአንድ ኪሎዋት ሰዓት 0 ነጥብ 01 አንድ የአሜሪካ ሳንቲም ያስከፍላሉ፡፡

በአንፃሩ ጎረቤት ኬንያ በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት 0 ነጥብ 22 የአሜሪካ ሳንቲም በማስከፈል ከመጨረሻ አንድ ደረጃ ብቻ ከፍ ብላ ኬፕ ቨርዴን ብቻ ቀድማ ውድ ታሪፍ ያላት ተብላ ተቀምጣለች፡፡

ማሊ፣ ሩዋንዳ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ጋቦን ውድ ታሪፍ ያላቸው ሀገራት ተብለው ሲቀመጡ በአንፃሩ ግብጽ፣ ናይጄሪያና ዛምቢያ በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት 0 ነጥብ 02 የአሜሪካ ሳንቲም በማስከፈል ኢትዮጵያ ከተመደበችበት ከቀዳሚው ምድብ ቀጥሎ ዝቅተኛ ታሪፍ ያላቸው ሀገራት ተብለዋል፡፡

በአፍሪካ የአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት ዝቅተኛው የኤሌክትሪክ ታሪፍ 0 ነጥብ 01 የአሜሪካ ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛውና ውዱ ደግሞ 0 ነጥብ 31 የአሜሪካ ሳንቲም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

“ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!”

Scroll to Top