አፍሪካ ኤሌክትሪክን ለማዳረስ የበጀት እጥረት ፈተና እንደሆነባት አንድ ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ

አፍሪካ ኤሌክትሪክን ለማዳረስ የበጀት እጥረት ፈተና እንደሆነባት አንድ ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ

የዓለማችን 1/5ኛ ህዝብ የሚኖርባት አፍሪካ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የበጀት እጥረት ፈተና እንደሆነባት ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጄንሲ አመለከተ፡፡

ኤጀንሲው የ2023 የዓለም ኢነርጂ ምልከታን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው አፍሪካ በ2030 የኤሌክትሪክን ተደራሽ ለማረጋገጥ፣ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማሟላትና ከኢነርጂ ጋር የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንቷን ከሁለት እጥፍ በላይ ማሳደግ ይጠበቅባታል፡፡

የአሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ለሁሉም አፍሪካውያን ንፁህ ኢነርጂ ተደራሽ ለማድረግ እ.ኤ.አ. ከ2026 ጀምሮ በየዓመቱ በአማካይ ሁለት መቶ ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ከነዳጅ ምርት ኤክስፖርት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ወጪያቸውን ለመተካት አልያም በብድር ለመሸፈን ጥረት እንደሚያደርጉ ቢገመትም በርካታ ሀገራት ግን ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደሚቸገሩ ሪፖርቱ ስጋቱን አስቀምጧል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በአፍሪካ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ህዝብ መካከል ግማሽ የሚሆኑት ወይም 600 ሚሊዮን ሰዎች ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ብርሃን አያገኙም፡፡

በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ሽፋን 43 በመቶ ላይ የሚገኝ ሲሆን ናይጄሪያ 86 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጎቿ ኤሌክትሪክ ባለማግኘት በቀዳሚነት ተቀምጣለች፤ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ለኃይል ማመንጫነት ሊውሉ የሚችል የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ቢሆኑምአብዛኛዎቹ ሀገራት ያላቸውን ፀጋ ወደ ኃይል ለመቀየት የበጀት እጥረት ከፍተኛ ፈተና ሆኖባቸዋል ይላል ሪፖርቱ፡፡

ይህን ለመቀየር ሀገራቱ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡

Scroll to Top