እያንዳንዷ ሴት ህልሟን በነፃነት የምትኖርበት ዓለም መፍጠር የጋራ ኃላፈነታችን ነው – ኢንጂነር ምትኩ ንጉሴ

እያንዳንዷ ሴት ህልሟን በነፃነት የምትኖርበት ዓለም መፍጠር የጋራ ኃላፈነታችን ነው – ኢንጂነር ምትኩ ንጉሴ

የደቡብ 1 ሪጅን ሠራተኞች እና አመራሮች 50 ኛውን ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በዓል አከበሩ።

በበዓል አከባበሩ ላይ ኢንጂነር  ምትኩ ንጉሴ እንደተናገሩት ማርች 8 በዓለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች ስኬት ፅናት እዲሁም ለእኩልነት የሚደረግ ቀጣይ ትግል የሚታወስበት ቀን በመሆኑ ከካላንደር በላይ የሆነ ኹነት ነው።

ሴቶች ያላቸውን እምቅ ችሎታ ለመጠቀም እና ለተቋም ዕድገት የበኩላቸው ን አስተዋጽኦ ለማሳደግ እንዲችሉ አወንታዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ በማድረግ እያንዳንዷ ሴት ህልሟን በነጻነት የምትኖርበት ዓለም መፍጠር የጋራ ኃላፊነታችን ነው ብለዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ የስርዓተ ፆታ ግንዛቤ  ማስጨበጫ ጸሁፍ አቅረዋል። 

ተቋሙ ሴቶችን ለአመራርነት ማብቃት   አወታዊ ድጋፍና ማበረታቻ እያደረገ መሆኑን ገልጸው ሴቶች ያለባቸውን ድርብርብ  ኃላፊነት በመቋቋም ራሳቸውን  ለስኬት ማዘጋጀት እንዳለባቸው ወ/ሮ ሌንሴ አሳሳበዋል።

Scroll to Top