እያንዳንዷን የውሃ ጠብታ በአግባቡ መጠቀም ይገባል

እያንዳንዷን የውሃ ጠብታ በአግባቡ መጠቀም ይገባል

የዝናብ እጥረትን ተከትሎ እያንዳንዷን የውሃ ጠብታ በቁጠባና ውጤታማ በሆነ መንገድ አገልግሎት ላይ ማዋል እንደሚገባ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ማስተባበሪያዎች ገለፁ።

የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን በ2018 አፈፃፀም እና በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በአዳማ ከተማ በጀመረው ውይይት ላይ የኃይል ማንጫ ጣቢያዎች ማስተባበሪያ 1 ዳይሬክተር አቶ አብዱ ይማም እንደገለፁት የዘንድሮውን ክረምት የዝናብ ሥርጫቱ አነስተኛ በመሆኑ በግድቦች በቂ ውሃ ላይኖር ስለሚችል የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከወትሮው በተለየ መልኩ መምራት ይገባል።

እያንዳንዷን ጠብታ ውሃ በቁጠባና ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀም ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ ሁሉም ሠራተኛ በከፍተኛ ተነሳሽነት የዕለት ከዕለት ሥራውን ሊያከናውን ይገባል ብለዋል።

የኃይል ማመንጫዎች ማስተባበሪያ 2 ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ገረመው በበኩላቸው የኃይል ማመንጫ ዩኒቶችን በወቅቱ በመጠገን ሁሉንም የማመንጫ ዩኒቶች ወደ አገልግሎት ማስገባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመለዋወጫ ዕቃዎችን በወቅቱ በማቅረብ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በሙሉ አቅማቸው ኃይል እንዲያመነጩ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኃይል ማመንጫዎች ማስተባበሪያ 3 ዳይሬክተር ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሽፈራው ናቸው።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top