ኢትዮጵያ የኃይል ማማ (Power Hub) የመሆን ጉዞዋን አፋጥናለች!

ኢትዮጵያ የኃይል ማማ (Power Hub) የመሆን ጉዞዋን አፋጥናለች!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኃይል ማመንጨት ዘርፍ አስደናቂ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች። አጠቃላይ ሀገራዊ የማመንጨት አቅማችን አሁን ላይ 9,760 ሜጋ ዋት (MW) ደርሷል፤ ይህም ለኢንዱስትሪዎቻችን ዕድገትና ለቀጣናዊ ትስስር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ይታመናል፡፡

🇪🇹የውሃ ኃይል ማመንጫዎቻችን ድርሻ
በኃይል ማመንጨት ሂደት ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት የውሃ ኃይል ማመንጫዎቻችን ሲሆን ከሚመነጨው 96% አስተዋጽዖ አላቸው፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD)፦ በ 5,150 MW ግዙፍ አቅሙ የኃይል ማመንጫችን በመሆን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ከመነጨው የ51% ድርሻ ነበረው፡፡

ጊቤ III (1,870 MW)፣ በለስ (460 MW) እና ሌሎችም የኃይል ማመንጫዎች እንደ ማመንጨት አቅማቸው ለኃይል አቅርቦቱ የራሳቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛሉ።

እያደገ የመጣው የንፋስ እና የሌሎች ታዳሽ ኃይሎች ድርሻ
የንፋስ ኃይል (~504 MW)፦ በአዳማ፣ በአሸጎዳ፣ በአይሻ እና በአሰላ የሚገኙ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ኢትዮጵያን በአፍሪካ የንፋስ ኃይል ቀዳሚ እያደረጓት ይገኛሉ።

♻️ ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ፡- በረጲ የተገነባው ከደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአፍሪካ የመጀመሪያው ጣቢያ ሲሆን ከኃይል ማመንጨት በተጓዳኝ የከተማዋን ቆሻሻ በማስወገድ ረገድ አርአያ የሆነ ተግባር እያከናወነ ነው፡፡

♨️🌋 ጂኦተርማል፦ በአሉቶ ላንጋኖ፣ በቱሉ ሞዬና በኮርቤቲ የሚከናወኑ የከርሰ-ምድር እንፋሎት ፍለጋዎች አዲስ የኃይል አማራጭ ይዘውልን እየመጡ ነው።

ቀጣይ ግባችን – የማመንጨት አቅምን 17,000 ሜጋ ዋት ማድረስ!
የሀገራችንን የኃይል አቅርቦት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በግንባታና በሂደት ላይ ይገኛሉ፦

ኮይሻ (1,800 MW) የውሃ ኃይል ማመንጫ፤
አይሻ I እና III የንፋስ ኃይል ፕሮጀክቶች
ቱሉ ሞዬ እና ኮርቤቲ የግል ባለሀብቶች (IPPs) የሚሳተፉባቸው ግዙፍ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

🇪🇹 ኢትዮጵያ የራሷን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት አስተማማኝ ኃይል በማቅረብ የቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር ማዕከል እየሆነች ነው። ይህ የሁላችንም ኩራትና የብልጽግናችን መሠረት ነው!

Scroll to Top