ኢትዮጵያና ቱርክ በኢነርጅ ዘርፍ ልማት አብሮ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ቱርክ በኢነርጅ ዘርፍ ልማት አብሮ ለመስራት ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ቱርክ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ በታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት እና በውሃ ኃይል መሠረተ ልማት ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

‎የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ እና የቱርክ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር ፈርመዋል።

‎በስምምነቱ መሠረት ሀገራቱ በታዳሽ ኃይል እና በኢነርጂ ቁጠባ ዘርፎች የጋራ ፕሮጀክቶችን እንደሚያዘጋጁ እንዲሁም የውሃ ኃይል ማመንጫ መሣሪያዎችን እና ተርባይኖችን በማምረትና በመትከል አብረው የሚሰሩ ይሆናል።

‎በተጨማሪም ቱርክ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ዘርፍ ፕሮጀክቶችን እንድታለማ እድል የሚፈጥር ነው።

‎የልምድ ልውውጥ በማጠናከር እና በተለያዩ ዘርፎች ተጨባጭ ፕሮጀክቶችን በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ሀገራቱ አረጋግጠዋል።

‎ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ትናንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ መምጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top