አዲስ የተገነቡት የዕቃ መጋዘኖች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለመዘርጋት ዕድል ፈጥረዋል

አዲስ የተገነቡት የዕቃ መጋዘኖች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለመዘርጋት ዕድል ፈጥረዋል

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገነቡት የዕቃ መጋዘኖች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለመዘርጋት ዕድል መፍጠራቸውን በተቋሙ የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ አስታወቀ፡፡

የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው እንዳስታወቁት ተቋሙ ለበርካታ ዓመታት ይጠቀምባቸው የነበሩትን ጠባብና አሮጌ የዕቃ መጋዘኖች የካይዘንና መሰል ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለመዘርጋት በሚያስችል ምቹ መጋዘኖች እየቀየረ ነው፡፡

አዲስ በተገነቡት መጋዘኖች ያለ አግባብ በየቦታው ተቀምጠው የነበሩ ዕቃዎችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ ከፀሐይ፣ ከአቧራ እና ከዝናብ መከላከል መቻሉን ተናግረዋል።

መጋዘኖቹ ብዛት ያላቸው የተለያዩ ዕቃዎች እንዲይዙ ተደርገው ከመገንባታቸውም በላይ የሙቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ የተገጠመላቸው መሆናቸውንም ነው የገለፁት።

በተቋሙ የዕቃ ግምጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈለቀ ክፍሌ እንደተናገሩት የዕቃ መጋዘኖቹ መገንባት ለሠራተኞች ምቹ የቢሮና የሥራ አካባቢ ፈጥረዋል፡፡

የሳፕ የአሰራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ቀልጣፋና ዘመናዊ የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች እንዲከናወኑ ማስቻሉንም ተናግረዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top