አካዳሚው ዲጂታል የምዘና ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ

አካዳሚው ዲጂታል የምዘና ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዲጂታል የምዘና ስርዓት መጀመሩን የኢትዮ ፓወር አካዳሚ አስታወቀ።

በአካዳሚው የዕውቀት አስተዳደርና ብቃት ምዘና ተወካይ ስራ አስኪያጅ አቶ ፈቃዱ አለማየሁ እንደተናገሩት ተቋሙ ከታህሳስ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የዲጂታል ምዘና ስርዓት በይፋ ጀምሯል።

የምዘና ሥርዓቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በ18 የሥራ መደቦች ለ91 የተቋሙ ሠራተኞች የዲጂታል ፈተና ያለምንም ችግር መስጠት መቻሉን ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ዙር የደረጃ ዕድገት እና ዝውውር ለሚወዳደሩ የተቋሙ ሠራተኞች በዋና መስሪያ ቤት፣ በደሴ፣ በሠመራ፣ በወላይታ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የዲጂታል ምዘና በስኬት መከናወኑንም ነው አቶ ፈቃዱ የገለፁት።

በቀጣይም ሌሎች የዲጂታል ምዘናዎች ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል።

የዲጂታል የምዘና ስርዓት ከዚህ ቀደም በሠራተኞች ይቀርብ የነበረውን የፈተና አወጣጥ የተአማኒነት ቅሬታ በእጅጉ እንደሚቀርፍ ታምኖበታል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top