አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ትኩረት ተሰጥቶት ተሰርቷል

አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ትኩረት ተሰጥቶት ተሰርቷል

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያልተቆራረጠ እና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች የፍተሻና ጥገና ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡

በዘርፉ የዕቅድና አፈፃፀም ክትትልና ትንተና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታገል ደገፋ የዘርፉን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ በ30 ሺህ 165 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የፍተሻ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ በ23 ሺህ 710 ኪሎ ሜትር መስመር ላይ ፍተሻ ተከናውኗል፡፡

ከፍተሻ ሥራው በተጓዳኝ የ24 ሺህ 716 ኪሎ ሜት የማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የጥገና ሥራ ለማከናወን ታቅዶ በ17 ሺህ 282 ኪሎ ሜርት ላይ ጥገና ማከናወን መቻሉንም በሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ከማስተላለፊያ መስመሮች በተጨማሪ በማከፋፈያ ጣቢያ ቤዮች ላይ የፍተሻና የቅድመ መከላከል ጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል።

በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በ8 ሺ147 ቤዮች ላይ የፍተሻ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ በ7 ሺ 351 ቤዮች ላይ ፍተሻ ሲከናወን በ8 ሺ 761 ቤዮች ላይ የቅድመ መከላከልና የጥገና ሥራዎች ለማከናወን ታቅዶ በ5 ሺ 774 ቤዮች ላይ መከናወኑን ነው የተናገሩት።

አፈፃፀሙ ከዕቅዱ ልዩነት ያሳየው በአንዳንድ አካባቢዎች በተስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች የተነሳ የፍተሻና የጥገና ሥራዎች በዕቅዱ መሠረት ለማከናወን ባለመቻሉ እንደሆነ አመልክተዋል።

አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የአቅም ውሱንነት ያለባቸውንና የቆዩ ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቅም የማሳደግና የማሻሻል እንዲሁም ግሪዱንና አስተማማኝ ለማድረግና ብሬከሮችን ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶት በመከናወን ላይ ይገኛል።

የአቅም ማሳደግና ማሻሻያ፣ በውጭ ስራ ተቋራጮች ሊከናወን የነበረ የስማርት ሜትር እና ዘመናዊ የመቆጣጣሪያ ብሬከሮች የተከላ ሥራዎችን በራስ አቅም ማከናወን መጀመሩ በዘጠኝ ወራት ከታዩ ጠንካራ ጎኖች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡

በአንፃሩ የሥራ ላይ ደህንነት መሳሪያዎች አለመሟላት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር አለመቻል፣ ከካሳ ክፍያ ጋር የተያያዙ ችግሮች በወቅቱ መፍትሄ አለማግኘታቸው በድክመት የሚጠቀሱ መሆናቸውም በሪፖርቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Scroll to Top