አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር የተከናወኑ ሥራዎች

አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር የተከናወኑ ሥራዎች


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስና የሲስተሙን ደህንነት ለመጠበቅ በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ እያከናወነ ያለው የቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤት እያሳየ ይገኛል።
 
ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፦
 
·        የብሬከር ማዘመን ሥራ፦ ከ2016 – 2018 ዓ.ም በነበሩት 3 ዓመታት  በ 60 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የነባር መቆጣጠሪያ ብሬከሮችን በዘመናዊ ብሬከሮች የመተካት ሥራ ተከናውኗል።
 
·        የአቅም እድገት፦ ቀደም ሲል የነበሩ ብሬከሮች ይሸከሙት የነበረው እስከ 5 ሜጋ ዋት የነበረ አቅም አሁን ባለው ማሻሻያ ከ10 እስከ 20 ሜጋ ዋት እንዲያድግ ተደርጓል። ይህም ለደንበኞች የሚቀርበውን የኃይል መጠን በእጥፍ አሳድጎታል።
 
·        የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ በዘይት ከሚሰሩና ለብልሽት ተጋላጭ ከነበሩ ነባር ብሬከሮች ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ቁጥጥር ሥርዓት በመሸጋገሩ የኃይል መቆራረጥ ርዝማኔ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
 
የመከላከያ ሥርዓት የማጠንከር ጅማሮ፦
·       ማከፋፈያ ጣቢያዎች በድንገተኛ ብልሽት ወቅት ራሳቸውን እንዲከላከሉ የሚያስችላቸውን የባትሪ ሥርዓት ለማጠናከር 51 የባትሪ ቻርጀሮች በአዲስ ተተክተዋል።
 ·        ከ3 ሺህ በላይ ነጠላ የባትሪ ሴሎች ተቀይረው ለጣቢያዎች አስተማማኝ የመከላከያ አቅም ፈጥረዋል።

ቀጣይ ዕቅዶች፦
·        በአሁኑ ወቅት በ 13 ተጨማሪ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የማዘመን ሥራው በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
 
·        በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጨማሪ 20 ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ለማዘመን ጥናት ተጠናቆ የግዥ ሂደት ላይ ይገኛል።
 
የማከፋፈያ ጣቢያዎችን ማዘመን የሚኖረው ጠቀሜታ
በማከፋፈያ ጣቢያዎች የሚከሰቱ የደህንነት ስጋቶችን በዘላቂነት በመፍታት፣ ለኢንዱስትሪዎችና ለነዋሪው ማህበረሰብ ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

Scroll to Top