ትናንት ማምሻውን በተፈፀመ ስርቆት አንድ ታወር ሲወድቅ በሀዋሳ ከተማ በከፊል ኃይል ተቋርጧል

ትናንት ማምሻውን በተፈፀመ ስርቆት አንድ ታወር ሲወድቅ በሀዋሳ ከተማ በከፊል ኃይል ተቋርጧል

ከይርጋለም ቁጥር 2 – ሐዋሳ ቁጥር 2 በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ጥምር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመበት ስርቆት ምክንያት አንድ ታወር መውደቁን የደቡብ 1 ሪጅን አስታወቀ።

በሪጂኑ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞሲሳ ገልቻ እንደገለፁት ስርቆቱ የማስተላለፊያ መስመሩ በሚያልፍበት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ ጨፌ በሚባል ቀበሌ በሚገኝ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የተፈፀመው ነው።

የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶው በተፈፀመበት ስርቆት ምክንያት በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 12:00 አካባቢ መውደቁን አቶ ሞሲሳ ተናግረዋል።

የተፈፀመው ስርቆት ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ብረቶቹን መልሶ ለመጠቀም እንኳ አስቸጋሪ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

እንደ ሥራ አስጂያጁ ገለፃ በስርቆቱ ምክንያት የሐዋሳ ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ ከይርጋለም ቁጥር 2 ማከፋፈያ ጣቢያ የሚያገኘው ኃይል የተቋረጠ ሲሆን የጣቢያው ኃይል የመስጠት አቅም በከፊል ቀንሷል፡፡

የወደቀውን ምሰሶውን ወደነበረበት ለመመለስ ሥራዎች መጀመራቸውንም የገለፁት አቶ ሞሲሳ የማስተላለፊያ መስመሩ ዳግም ኃይል ማስተላለፍ እስኪጀምር ድረስ በከፊል ኃይል የተቋረጠባቸው ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top