ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኃይል ማመንጨት አፈጻጸም አስመዝግቧል።
የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ከማል አህመድ እንደገለጹት ግድቡ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 13 ሺህ 778 ነጥብ 37 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የዕቅዱን 95.7 በመቶ አሳክቷል!
ይህ ስኬት በቁጥር ሲታይ፦
✅ የ122% ብልጫ፦ የዘንድሮው የማመንጨት አቅም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ122 በመቶ ታላቅ ብልጫ አሳይቷል። (ባለፈው ዓመት 6 ሺህ 213 ጊጋ ዋት ሰዓት ነበር)።
✅ የ51% የሀገር ድርሻ፦ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ እንደ ሀገር ከመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ብቻውን 51 በመቶ ድርሻ አለው!
✅ የተርባይኖች መጨመር፦ ለዚህ ከፍተኛ ስኬት ዋነኛው ምክንያት ወደ ሥራ የገቡ ተርባይኖች ቁጥር መጨመር ነው።
✅ የውሃ ከፍታ፦ ባለፉት ወራት የግድቡ የውሃ ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 629.1 ሜትር ደርሶ ቆይቷል።
ቀጣይ ዕቅድ
በቀጣዮቹ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ቀናት ውስጥ ተጨማሪ 4 ሺህ 700 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት፣ በዓመቱ የታቀደውን 18 ሺህ 477 ነጥብ 6 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
ይህ ውጤት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የብርሃን ጉዞ እየመራ መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ሌላኛው የታሪክ ምዕራፍ ነው!