ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ፋይናንስ የተሰራ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ፋይናንስ የተሰራ ነው

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ትብብር ያለምንም የውጭ ብድር እና እርዳታ የተገነባ መሆኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር እንደገለጹት በተለያዩ አካላት የግድቡ ወጭ በሦስተኛ ወገን እንደተሸፈነ ተደርጎ የሚተላለፈው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡

በዚህም ከሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ አባላት የቦንድ ሽያጭ እና ስጦታ ከ23 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ለግድቡ ግንባታ መዋሉንና ቀሪው ደግም በመንግስት መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ የተገነባ የዚህ ትውልድ የወል ትርክት ሆኖ የተመዘገበ የዘመናች ዓድዋ ነው ብለዋል።

የግድብ ግንባታው በአሁኑ ወቅት እየተጠናቀቀ መሆኑን በመግለፅ ይህም ከተባበርን በራስ አቅም ፕሮጀክት መቅረጽና መምራት እንዲሁም በሕብረት ጀምረን ማጠናቀቅ እንደምንችል ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ ማምረት ሲጀምር 5 ሺ 150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በዋናነት ፋይናንስ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑን ጠ/ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መናገራቸው ይታወሳል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top