በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

በ2018 ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ እንደገለፁት ውይይቱ እንደሀገር በበጀት ዓመቱ ለማከናወን የታቀዱ ሥራዎችን እና ዕቅዱን ለማሳካት ከሰራተኛው የሚጠበቀውን ሚና ለማሳወቅ ያለመ ነው።

ተቋሙ እንደ ሀገር የተያዙ ዕቅዶችን በማሳካት በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው በመረዳት ሁሉም የሥራ መሪና ሠራተኛ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርበት ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።

በአሁኑ ወቅት በበጀት ዓመቱ እንደ ሀገር በሁሉም ዘርፎች ለማከናወን የተያዘው ዝርዝር የዕቅድ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top