በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ የተመራ የተጽዕኖ ፈጣሪ የአፍሪካ መሪዎች ልጆች እና ግለሰቦች ልዑካን ቡድን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጎብኝት እያካሄዱ ነው።
ሚኒስትር ዲኤታው አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የጉብኝቱን ዋና ዓላማ አስመልክተው እንደገለጹት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦቹ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማመንጫ ጣቢያ ነባራዊ እውነታን እንዲረዱና ትክክለኛ መረጃ እንዲያጋሩ ለማስቻል ነው።
በጉብኝቱ ዲሴንደንት በሚል ማህበር የተቋቋሙ የቀድሞ ታዋቂ የአፍሪካ መሪዎች ልጆች በጉብኝቱ ላይ የተገኙ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው ይህም አባቶቻቸው ሲመኙት የነበረውን አፍሪካውያን ጀምሮ የመጨረስ ህልም በህዳሴ ግድቡ የተሳካ መሆኑን እንዲመለከቱ ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
ታዋቂው የጋና የነጻነት ታጋይ ክዋሚ ንኩርማ ልጅ ሳሚያ ንኩሩማን ጨምሮ የኬኔት ካውንዳ፣ የጁሌስ ኔሬሬ እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች መሪዎች ልጆች እንዲሁም የተለያዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል።
በተጨማሪም ከቱሪዝም ሚኒስትር፣ እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኃይል የተውጣጡ አመራርና ሠራተኞች በጉብኝቱ ታድመዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”






