ተንቀሳቃሸ ማከፋፈያ ጣቢያው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ተጨማሪ አቅም ፈጥሯል

ተንቀሳቃሸ ማከፋፈያ ጣቢያው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ተጨማሪ አቅም ፈጥሯል

የገፈርሳ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በቅርቡ ወደ ሥራ ያስገባዉ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለደንበኞች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ተጨማሪ አቅም መፍጠሩን የጣቢያዉ ኃላፊ አስታወቁ።

ኃላፊዋ ወ/ሮ አበበች ሸዋለም እንደገለፁት ጣቢያው በ230 ኪሎ ቮልት ከፊንጫ፣ ጌዶ 1 እና 2፣ ሰበታ፣ ሱሉልታ እና ሸጎሌ በስድስት ገቢ መስመሮች ኃይል ያገኛል፡፡

ጣቢያዉ በሁለት ባለ 50 እና ሁለት ባለ 25 ሜጋ ቮልት አምፔር ኃይል ፓወር ትራንስፎርመሮች ኃይል እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች የኃይል ፍላጎት ለማሟላት በቅርቡ ወደ ሥራ የገባው ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ በ15 ኪሎ ቮልት በገፈርሳ ዙሪያ ለሚገኙት አካባቢዎች ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝ ኃላፊዋ ተናገረዋል።

እንደ ኃላፊዋ ገለፃ ተንቀሳቃሽ የማከፋፈያ ጣቢያው በዙሪያው ያሉ ግለሰብ የኃይል ተጠቃሚ እና የንግድ ቤት ደንበኞችን ጨምሮ በዙሪያው የሚገኙ ከ400 በላይ ትንንሽና ትልልቅ አምራች ኢንደስትሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተጨማሪ አቅም ፈጥሯል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top