ማከፋፈያ ጣቢያዉ የአካባቢዉን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ እየሰራ ነዉ

ማከፋፈያ ጣቢያዉ የአካባቢዉን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ እየሰራ ነዉ

የቱለፋ ባለ 132/33 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአካባቢዉ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች እና ለነዋሪዎች የኃይል ፍላጎት ተደራሸ ለማደረግ እየሰራ መሆኑን የጣቢያዉ ኃላፊ አስታወቁ።

የጣቢያው ኃላፊ አቶ አዲሱ ከፍአለ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዉ በአካባቢዉ ያለዉን የኢንቨስትመንት ፍሰት መሰረት አድርጎ በ2012 ዓ.ም ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።

ጣቢያዉ በ132 ኪሎ ቮልት የተቀበለውን ኃይል 50 ሜጋ ቮልት አምፔር ኃይል የመሸከም አቅም ባለው ትራንስፎርመር አማካኝንት ለቡልጋ ከተማ፣ አሌልቱ፣ ጨፌ ዶንሳ፣ ሰንዳፋ እና ሸኖ ከተሞችና አካባቢያቸው ኃይል እየሰጠ እንደሚገኝ አቶ አዲሱ ተናግረዋል። 

እንደ ኃላፊው ገለፃ ጣቢያው በአካባቢው ያለውን የኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት መሰረት አድርጎ የተቋቋመ በመሆኑ በቡልጋ ከተማ መስተዳድር እና አካባቢዉ የተሰማሩ 59 ፋብሪካዎችን የኃይል ተጠቃሚ ማደረግ ችሏል።

በሌላ በኩል ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያዉ በደብረ ብርሃን ቁጥር ሁለት እና ለገጣፎ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች መካከል ላይ በመገኘቱ የኃይል መቆራረጥ ሲያጋጥም በቅንጀት በመስራት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መቻሉንም አክለዋል።

በአካባቢዉ የሚስተዋለውን የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና የኃይል ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የማከፋፈያ ጣቢያ ለመገንባት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top