በአካባቢዉ ለተሰማሩ የኢንቨስትመት ዘርፎች በበቂ ሁኔታ ኃይል እየቀረበ ነዉ

በአካባቢዉ ለተሰማሩ የኢንቨስትመት ዘርፎች በበቂ ሁኔታ ኃይል እየቀረበ ነዉ

በቡራዩ ከተማ እና አካባቢው የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎትን ያገናዘበ በቂ አቅርቦት መኖሩን የከተማው ምክትል ከንቲባ አስታወቁ።

ምክትል ከንቲባው አቶ ሽብሩ ዓለሙ እንደተናገሩት በቡራዩ ከተማ እና አካባቢዉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ከተሰማሩ 356 ባለሀብቶች መካከል 276ቱ ወደ ምርት የገቡ ሲሆን 86ቱ ሥራ ለመጀመር በሂደት ላይ ናቸዉ፡፡ 

የኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት የማይተካ ሚና እንዳለው የጠቀሱት ምክትል ከንቲባው አቶ ሽብሩ ከተማዋ ለኢንደስትሪ ተመራጭ በመሆኗ ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት እንደሚያስፈልጋት ጠቁመዋል።

60 ዓመታት ያስቆጠረው የገፈርሳ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አቅሙን በማሳደግ ያከናወናቸዉ ተግባራት እያደገ የመጣዉን የኃይል ፍላጎት ለመመለስ አስችሎታል ብለዋል። 

በቡራዩ ከተማ እና አካባቢዉ ለሚገኙ ከ270 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ ለበርካታ የአካባቢዉ  ነዋሪዎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top