ተንቀሳቃሸ ማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢዉ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ችግር ፈቷል

ተንቀሳቃሸ ማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢዉ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ችግር ፈቷል

የጉደር ባለ 132/15 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአምቦ ከተማና አካባቢዉ የነበረውን የኃይል አቅርቦት ችግር በመፍታት ለኢኮኖሚ እድገትና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአምቦ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ጅፋራ እንደገለፁት ከዓመታት በፊት በአካባቢው የነበረው የኃይል እጥረትና መቆራረጥ በኢንዱስትሪዎች፣ በፋብሪካዎችና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ነበር፡፡

በአካባቢዉ የተገነባው ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአካባቢው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ መነቃቃትን መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በመኖሩ ከነባር ተቋማት ባለፈ አዳዲስ ባለሀብቶችን ወደ ከተማዋ ለመሳብ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን ለማፋጠን ማስቻሉንም አቶ ደረጀ አስረድተዋል፡፡

የኃይል አቅርቦቱ አስተማማኝነት በቅርቡሥራ የጀመረው የከተማ አስተዳደሩ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽዖ ማድረጉን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጉደር ከተማ እና አካባቢው ያለውን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ ሥራ በማከናወኑ የከተማ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አመስግነዋል፡፡

በቀጣይም ተቋሙ ማንኛዉንም የማስፋፊያ ሥራ ሲያከናውን ከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግና ከተቋሙ ጋር ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

Scroll to Top