ተቋማቱ የታሪፍ ክለሳ ጥያ ቄ ከማቅረባቸው በፊት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃ በሙሉ ወስደዋል

ተቋማቱ የታሪፍ ክለሳ ጥያ ቄ ከማቅረባቸው በፊት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃ በሙሉ ወስደዋል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የታሪፍ ክለሳ እንዲደረግ ለመንግስት ጥያ ቄ ከማቅረባቸው በፊት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች በሙሉ መውሰዳቸውን የታሪፍ ክለሳ የጥናት ቡድኑ አስታወቀ።

የጥናት ቡድኑ አባልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ መንግስቱ እንደገለፁት ተቋማቱ አፈፃፀማቸውን ለማሻሻል የውስጥ አሰራራቸውን ማዘመንና ወጪ መቀነስ ላይ ትኩረት አድረገው ሲሰሩ ቆይተዋል።

የተቋማቱን የፋይናንስ ጤናማነት ማሻሻል፣ ብድርን ወደ መንግስት ማዞር፣ ከመንግስት ቀጥታና ተዘዋዋሪ ድጋፍ ማግኘትና ሌሎች ተጨማሪ ርምጃዎች መወሰዳቸውን አቶ ዓለማየሁ ተናግረዋል።

ከሀገር ውስጥና ከውጭ አበዳሪዎች በአነስተኛ ወለድ የሚገኘውን ብድር በመጠቀም ተቋማቱ አዳዲስ መሰረተ ልማት ሲገነቡ፣ አቅም የማሳደግ ስራ ሲሰሩና አገልግሎቱን ሲሰጡ እንደቆዩ ጠቁመዋል።

በቀጣይ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠትና ተደራሽነትን ለማስፋት በማሰብ የታሪፍ ክለሳ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

“ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!”

Scroll to Top