ተቋሙ ያገለገሉ ንብረቶችን በዲጂታል ሥርዓት ሊያጫርት ነው

ተቋሙ ያገለገሉ ንብረቶችን በዲጂታል ሥርዓት ሊያጫርት ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በዲጂታል ሥርዓት ለማጫረት የሚያስችል ስምምነት ከኦክሽን ኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመ።

ሥምምነቱን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል  በኩል የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው እና በኦክሽን ኢትዮጵያ በኩል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ዮሴፍ አንኩ ተፈራርመዋል፡፡

ሥራ አስፈፃሚዋ ወ/ሮ ስመኝ አያሌው እንደተናገሩት ስምምነቱ ተቋሙ ያገለገሉ ንብረቶቹን ለማስወገድ የሚያደርገውን የማኑዋል  የጨረታ ሂደት ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለመቀየር የሚስችለው ነው፡፡

አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን ለማስወገድ ተቋሙ የሚያደርገውን አድካሚ ሂደት፣ ጊዜን እና ወጪን ቆጣቢ በሆነ መልኩ በማዘመን  ለማቀላጠፍ  ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ሀገር በቀል የዲጂታል አጫራች ድርጅቱ ጨረታዎችን በማውጣትና ተደራሽነቱን በማስፋት በአጭር ጊዜ  ተቋሙ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንደሚያስገኝ እምነታቸውን ገልፀዋል።

የጨረታ ሂደቱ ከሰዎች ድርድር እና ንከኪ የጸዳ፣ ለብልሹ አሰራር የማያጋልጥ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ ያሉ ተጫራቾች በእኩልነት ለማሳተፍ የሚያስችል እና አገልግሎቱን ለመጠቀም ምንም ዓይነት ወጪ የማያስወጣ በመሆኑ ተመራጭ እንደሆነ ወ/ሮ ስመኝ አስረድተዋል፡፡

የሀገር በቀሉ የዲጂታል አጫራች ድርጅት የኦክሽን ኢትዮጵያ  ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዮሴፍ አንኩ በበኩላቸው ድርጅታቸው  በጨረታ የሚሸጡ  ንብረቶች በዲጂታል ሥርዓት ተደራሽ በማድረግ ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ32 ሺህ በላይ ተጫራቾችን እና ከ500 በላይ አጫራቾች ድርጅቶችን ይዞ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ባለይ ማገበያየቱን ገልፀዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top