ተቋሙ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

ተቋሙ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚያስተዳድራቸውን የኃይል መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መገምገም ጀምሯል።

በኃይሌ ግራንድ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የግምገማ መድረክ ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻን ጨምሮ ሁሉም የማኔጅመንት አባላት፣ የፕሮጀክት ዳይሬክተሮችና ሥራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

በበጀት ዓመቱ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን፣ የአይሻና የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ በርካታ የማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ማስተላለፊያ መስመሮችን አጠናቆ በማስመረቅ ረገድ ትልልቅ ስኬቶች መመዝገባቸው በግምገማው መጀመሪያ ላይ ተገልጿል፡፡

ይህ የግምገማ መድረክ ባለፉት 11 ወራት በፕሮጀክት አፈጻጸም ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

እንደ ተቋም ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ፣ በጀትና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ ከሪፖርት ባለፈ በተግባር የተደገፈ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ መሰል መድረኮች አስፈላጊ መሆናቸውም ተብራርቷል።

በአሁኑ ወቅት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሌሎች ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በዝርዝር እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን እኛም ሂደቱን እየተከታተልን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

Scroll to Top