ተቋሙ የነደፈውን ዕቅድ ለማሳካት የሴቶችን እምቅ አቅም ሊጠቀም ይገባል

ተቋሙ የነደፈውን ዕቅድ ለማሳካት የሴቶችን እምቅ አቅም ሊጠቀም ይገባል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራርና ሠራተኞች በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ113ኛ፣ በአገር አቀፍ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን “ሴቶችን እናብቃ፤ ሰላምና ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በተቋም ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡

በመርሀግብሩ ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ባስተላለፉት መልዕክት በተቋሙ ሁሉም የሥራ ክፍሎች ያሉ ሴቶችን ተሳትፎ የሚገድቡ ማናቸውንም እንቅፋቶች በማስወገድ የሥራ ቦታዎች ከጾታ መድሎ የጸዱ፣ አካታችና አሳታፊ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሴቶች ችሎታቸውን እንዲያጎለብቱ ዕድል መስጠቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ኢንጂነር አሸብር አንድ ተቋም የሚጠበቅብንን ስኬት ለማስመዝገብ የሴቶችን እምቅ አቅም መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተቋም ደረጃ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር የተቋሙ ሴት ሠራተኞች በሁሉም ዘርፍ ራሳቸውን እንዲያሳድጉና አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት በማስቀጠል ሊሆን እንደሚገባል ገልፀዋል፡፡

በዓሉን የተመለከተ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት በተቋሙ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መመሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ በበኩላቸው ሴቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል።

በጽሁፉ ሴቶች ሥለራሳቸው ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ እምቅ አቅማቸውን የሚጠቀሙበትን አውድ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን በጽሁፋቸው አመልክተዋል፡፡

በተቋሙ የሴቶችን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለሴቶች በቅጥር፣ በልዩ ልዩ ሥልጠናዎች፣ በነጻ የትምህርት እድል እና በደረጃ ዕድገት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው በሕብረት ስምምነቱ መካተቱን በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

ተቋሙ እየተገበረ ባለው የስትራቴጅክ ዕቅድ ላይ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎች ታቅደው እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዝግጅቱ ተሳታፊዎችም በተቋሙ የህፃናት ማቆያ መቆቋሙ የሴቶችን ጫና በማቃለል በኩል ያለውን መልካም ጅማሮ አድንቀው በቀጣይ በተቋም የሴቶችን ተጠቃሚነትና የአመራር ሰጭነት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top