ተቋሙ ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋትን ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊኖረው ይገባል

ተቋሙ ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋትን ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊኖረው ይገባል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢትየጵያ በቀጣይ 10 ዓመት የሚያስፈልጋት ኢነርጂ ታሳቢ ያደረገ ስትራቴጂ ሊቀርፅ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሳሰቡ፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዶ/ር ብሪክ ታዬ የተቋሙ የግማሽ በጀት ዓመት ግምገማ ሲጠናቀቁ በሰጡት አቅጣጫ እንዳመለከቱት የተቋሙ ስትራቴጂ ሀገሪቱ የምትፈልገውን ኢነርጂ ለያሟላ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ግልጽ ውይይት ሊደረግበት ይገባል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በትልቅ መስዋዕትነት ውጤት የተገኘበት መሆኑን እንረዳለን ያሉት ሥራ አስፈፃሚው ህዝብ እና መንግስት በጋራ ሲሰራ እንዲህ ዓይነት ውጤት ማምጣት እንደሚችል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ህዳሴ የተሰራበት የፕሮጀክት አስተዳደር ዕውቀት እና ሂደት በቀጣይ ለሚገነቡት ፕሮጀክቶች መማሪያ ስለሚሆኑ ተሰንደው መቀመጥ እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ህዳሴን ከማስመረቅ በተጨማሪ ተቋሙ በፋይናንስ ላይ ያስመዘገበው ውጤት ተቋሙን ወደተሻለ መንገድ እንደሚመራው እምነት እንዳላቸው ጠቅሰዋል፡፡

ለኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የፋይናንስ አቅርቦት ለማመቻቸት የተለያዩ አማራጮች እየታሰቡ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ ጠቅሰዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top